አምልኮተ እግዚአብሔር  በዶ/ር አቤኔዘር ሳሙኤል 09/29/24

 አምልኮተ እግዚአብሔር  በዶ/ር አቤኔዘር ሳሙኤል 09/29/24

  • የአምልኮተ እግዚአብሔር  መሰረትም አድራሻም ራሱ እግዚአብሔር ሲሆን፥ ቤተክርስቲያንም አምልኮን በተመለከተ  አግላይ ናት።
  • ስለ አምልኮ ለምን ማወቅ  ያስፈልጋል?

  1.  የሀይማኖት ልብ ስለሆነ:-  የእግዚአብሔር መጥራት  ማዕከላዊ ሃሳብ  እኛን የእርሱ ካህናት ለማድረግ ስለሆነ ( ዘፀ 19:5፣ 1 ጴጥ 2:9) 
  2. ዘመናችንን ከመመርመር አንፃር:-  የዘመን  ሙጣጭ ላይ እንዳሉ ሰዎች ወደ ገደል እንዳናመራ እንድንጠነቀቅ ያደርገናል  (ሉቃ 12:54-56፣ 2 ጢሞ 3:1-5)።

  • እግዚአብሔር ለክብሩ ቀናተኛ ነው። ለራሱም  ቅሬታዎችን በዘመናት መካከል ያስቀራል (ኢሳ 42:8፣  1 ነገ 19:18)።
  • ሰይጣን አሁንም ቤተክርስቲያንን ወድቀሽ ስገጂ፥  የዓለምን ክብር ሁሉ እሰጥሻለሁ እያለ ያባብላታል  (ማቴ 4:8-10)።
  • ስግደት (Greek- proskuneo (προσκυνέω))የአምልኮን መሰረታዊ ምንነት ያሳየናል። ይኸውም ክብርን መጣልን፥ መሸነፍን፥ እጅግ ትልቅ በሆነ ማንነት ፊት መውደቅን፥ ዝቅ የማለት የአድናቆት ምላሽን ያመለክታል (ዮሐ 4:19 21-24)።
  • ስግደት የሚጀምረው ከልብ ነው (1 ነገ 11:9)።
  • አምልኮን እውነት የሚያደርገው የምንሰግድለትን ማወቅ ነው። ቤተክርስቲያን ስለምታመልከው ስለ እርሱ ግልጽ እና ጤናማ አስተምህሮ ከሌላት አምልኮ ፍሬያማ አይሆንም።
  • አምልኮን በተመለከተ መፅሀፍ ቅዱስ አራት መሰረታዊ ነገሮችን ያስተምረናል። እነዚህም-

  1. እግዚአብሔር ቅዱስ ነው።  ይህም ማለት እርሱ አምሳያ ወይም እኩያ የሌለው፥ ከማንም ጋር  ለውድድር  ወይም ለንጽጽር የማይቀርብ፥ ከፍጥረቱ  ሁሉ የተለየ ነው (ኢሳ 6:1-4፣ ኢሳ 40:25)።
  2. የምናመልከው እግዚአብሔር ስሉስ አሀዱ አምላክ ነው።  ነገርን ሁሉ ከመፍጠሩ በፊት በራሱ ውስጥ ግንኙነት ያለው፥ አንዱ አካል ሌላውን የሚያከብር፥ የሚወድ አምላክ ነው።  እኛንም የጠራን ከዚህ ግንኙነት እንድንካፈል ነው (ኤፌ 2:18፣ 1ዮሐ 1:3፣ 1ዮሐ 14:23)።
  3. እግዚአብሔር  እጅግ ከፍ ያለ ቢሆንም በጣም ቅርብ አምላክ ነው። ለምንሰጠው አምልኮ  ምላሽ የሚሰጥ አምላክ ነው። በዚህ ልንደሰትም ደግሞም ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል (ኢሳ 66:3፣ ዕብ 12:28)።
  4. የምናመልከው እርሱ በራሱ ሙሉ የሆነ አምላክ ነው።  ከራሱና በራሱ ህይወት የሚኖር፥ ደጋፊ የማያስፈልገው፥ ከትርፉ ለኛ የሚያፈስ ነው (ሐዋ 17:24-28)።

  • እግዚአብሔርን ልናመልክ ስንመጣ የልባችንን ጭንብል  ልናወልቀው ይገባል። እኛ የተጠራነው በቅንነት ልባችንን እንድናፈስለት ነው (ዕብ 10:21)።
  • አምልኮ፥ የእግዚአብሔር አዳኝነት (ትድግና) የመጨረሻ መገለጫ ከሆነው ከታረደው በግ ጋር፥ ታስሮ ሊቀርብ ይገባል (ራዕ 5:6፣9)። የንጋት ኮከብ የሆነው ኢየሱስ በአምልኳችን ሁሉ ሊደምቅ ያስፈልጋል። እርሱ የአምልኳችን ተቀባይ ብቻ ሳይሆን የአምልኳችን መሪ ነው። 
  • የአምልኳችን ይዘት የእግዚአብሔርን ፈጣሪነት እና የማንነቱን ልዩነት ሊያካትት ይገባል (ዮሐ 4:10)።
  • እግዚአብሔርን እንዴት እናምልከው?

  1. በእምነት-  እግዚአብሔር እንዳለ እና መሰዋዕትን የሚቀበል  መሆኑን በማመን (ዕብ 11:4)
  2. ራሳችንን እየቀደሰን- ከሀጥያት በመራቅ፥ በመንጻት (ዕብ 12:14)
  3. በትህትና 
  4. በፍቅር (መዝ 84:1-2፣10)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *