ዘላለማዊ ስጦታ 

ዘላለማዊ ስጦታ 

2 ቆሮ 9: 13-15  “ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን። ”

በምድር ውስጥ የምንሰጠውና የምንቀበለው ስጦታ ሁሉ ዋጋው ከጊዜ ወደ ጊዜ ይወርዳል:: ከእግዚአብሔር ዘንድ የማይለወጥ ፣ የማይቀንስ የማይደበዝዝ ፣ ዘላለማዊ ስጦታ ተሰጥቶናል::
የተሰጠን ዘላለማዊ ስጦታ ምንድነው ? ኢየሱስ ነው !! 
ሰጪውስ ማን ነው ? እግዚአብሔር ነው !!
1 ዮሐንስ 3:16
ምክንያቱስ ምንድነው ? ስለ ኃጢአታችን ማስተሰሪያ እንዲሆነን 1 ዮሐንስ 4:10 ሮሜ 6 :15 

ይህ ስጦታ ማነው? 

1. እየሱስ የቀደመውና የተገለጠው የጸጋ ስጦታችን ነው ። ቲቶ 2: 11-12
2. ወደ አብ የምንገባበት ብቸኛ በር ነው ። ዮሐንስ 3:3
3. እርሱ እውነት  ህይወት መንገድ ነው ። 
4. ከእግዚአብሔር የተቀበልነው የነፍሳችን እረፍት ነው ።  ማቲዎስ 11 :29 
5. እርሱ ጽድቃችን ነው። ሮሜ 3:21 ገላትያ 3:13 
6. እርሱ ቅድስናችን ነው። 1 ቆሮ 6:9-11
7. እርሱ የደስታችን ምንጭ ክብራችን ውበታችን ነው።
8. እርሱ የበረከታችን ሁሉ ባለቤት ነው። ኤፌ1:3 ማቴ 6:33

ስለዚህ ራሱን ባዶ ስላደረገውን፣  አምላክ ሆኖ ሳለ  ስጋን ለብሶ ስለመጣው፣  ነፍሱም ስለእኛ አሳልፎ ስለሰጠው፣  ሙታን ሆነን ሳለን ህይወትን ስለሰጠንን፣ ክፉዎች ሆነን ሳለን መልካምን ስላደረገልን፣  እርግማናችንን በጽድቅ ለቀየረልን፣  ከአይምሮአችን በላይ ስለሆነው ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *