የቀድሞውን ፍቅር ማደስ: በወንድም አመሃ በዬቻ  9/22/23 

የቀድሞውን ፍቅር ማደስ: በወንድም አመሃ በዬቻ  9/22/23 

    • ብዙ ጊዜ በእግዚአብሔር ቤት ዕድሜ ስንቆጥር የቀደመው ፍቅራችን እየቀነሰ ከፍልቅልቅ ህይወት ይልቅ በትዝታ ብቻ መኖር እንጀምራለን ራዕይ 2:4)።አንድን አማኝ ጠላታችን ዲያብሎስ ከክርስቶስ ኢየሱስ  ሊለይ ስለማይችል በፈተና ጋጋታ ሊያዘል ወይም ሊያደክም ዘወትር ሳያቋርጥ ይጥራል።ዩሐ 10:28ስለዚህም ክርስቲያን ዘወትር በመንፈስ ቅዱስ ሃይል የተነቃቃ መሆን አለበት ( መሳ 13:25)።

የሚከተሉትን አራት ጥያቄዎች ራሳችንን በመጠየቅ ያለንበትን ሁኔታ መገምገም  እንችላለን:- 

1) በዓለም ካሉ ነገሮች ይልቅ ጌታ ኢየሱስን አብልጠን እንወደዋለን ወይ (ማር 12:30) 

2) ከሁሉ በፊት የእግዚአብሔርን መንግስት  እናስቀድማለን ወይ (ማቴ 6:3)

3) በህይወታችን የመንፈስ ቅዱስ ሃይል ይገለጣል ወይ (ሐዋ 1:8 ሉቃ 24:40)

4) ከወንድሞች እና ከእህቶች ጋር በፍቅር እንኖራለን ወይ (ማር 12:30 ገላ 5:22)

መነቃቃት ለክርስቶስ የነበረንን የቀድሞውን ፍቅር ማደስን፣  ወደኋላ እየሄደ (እያሽቆለቆለ) ከነበረው ህይወታችን በመውጣት ከኢየሱስ ጋር ጤናማ ወደሆነ ህብረት (ግንኙነት) መመለስን ያካትታል።

መነቃቃት  እንዴት ይመጣል?

1)  ኃጢአተኛ መሆናችንን መገንዘብ

2) መንፈስ ቅዱስ የገለጠልን ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት መናዘዝ ስንችል (ምሳ 28:13፣  1ዮሐ 1:9)

3) የበደሉንን ሁሉ ይቅር ስንል  (ማቴ 5: 23:24፣  ሉቃ 19:8)

4) ህይወታችንን ለክርስቶስ ስናስገዛ 1 ቆሮ 6: 19-20

5) ንስሐ የሚገባ ትሁት ልብ ሲኖረን ልባችንን ከፍተን ለመንፈስ ቅዱሰ መስጠት (ኤፌ5:18 ሉቃ 11:13

6) ለመንፈስ ቅዱስ በመታዘዝ መኖር ገላ 2:20 ሮሜ 8:29

የተጠቀሱትን የልብ ዝግጅቶች ካደረግን በኋላ የመነቃቃቱን ሥራ በሙሉ የሚሰራው መንፈስ ቅዱስ ነው ።  ይህንንም የሚያደርገዉ በራሱ መንገድና ጊዜ ነው። ሰለዚህ መንፈስ ቅዱስን በመጠበቅ፣  በመሻት  ለ‍እንተጋ  ያስፈልጋል።

2 ዜና 7:14፤ በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢልፈጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *