ቤቴል ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ሪትሪት: የጌትነቱ ኃይል

ቤቴል ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ሪትሪት: የጌትነቱ ኃይል

ክፍል –  የመንፈስ ቅዱስ ኃይል አስፈላጊነት

  • ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለሦስት ዓመት ሲያሰለጥናቸው ከቆየ በኋላ፣ ሞቱ በቀረበ ጊዜ ባጠገቡ ሆነው የተማሩትን የሚተገብሩበት የፈተና ሰዓት ደረሰ (ዮሐንስ 18:1-12) ። ጴጥሮስም መምህሩን ይወደውና፣ ሊያገለግለው ይፈልግ ስለነበረ ወደ ጌታው የሚመጣውን መከራና ጥቃት ለመከላከል ሲል በስጋ ሃይል ተነሳ። ኢየሱስ ግን በጽዋ ውስጥ ካለው መራራ ነገር ባሻገር ጽዋውን የያዘውን የአብን አጅ ተመልክቶ እራሱን ለአብ ሃሳብ አስገዛ (ዮሐንስ 18:11)።

  • የጴጥሮስ ሀሳብ ኢየሱስን ለማገልገል ቢሆንም የስጋ መንገዱ የአብን እጅ የሚገፋ ስለነበረ የአብ ጠላት (የዲያብሎስ ወገን) ሆኖ ተገኘ (ሉቃስ 22:49-51፣ማቴዎስ 26:51-54)።

  • ለጌታ ያለን ቅንዓት አስፈላጊ ነዉ፤ ነገር ግን በቂ አይደለም። ፍላጎት ያለ እግዚአብሔር ኃይል ከፍተኛ ጥፋት ያመጣል። የእግዚአብሔር ስራ በእግዚአብሔር ኃይል ብቻ ይሰራል (ሉቃስ 24:49)።

  • መንፈስ ቅዱስ የወረደው በተራቡት እና በተጠሙ ሁሉ ላይ ነው (ሐዋ 2:1-4)። ቅንዓት እና መንፈስ ቅዱስን በአንድነት መጠማት ሲገናኙ ልብና ተግባር አንድ ሆነው ኢየሱስን ያከብራሉ (ሐዋ 2:14-40)። 

  • ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ለመሞላት ምን አይነት መሠረታዊ መረዳት ያስፈልገናል?

ክፍል – ኢየሱስ የቤተክርስቲያን አናጺ

  • ኢየሱስ የቤተክርስቲያን መሠረት ብቻ ሳይሆን ባለቤትና አናጺ (ገንቢ) ነው (1 ቆሮ 3:10-11)።

  • ለኢየሱስ በምድር ላይ ያለው ሀብቱ ደሙን አፍሶ የገዛው፣ የመከራው ጭማቂ የሆነው ህዝቡ ነው (ዮሐ 21:15-17) ። ይሄ ህዝብ ሰማይ ለላከው ተልዕኮ ፍጻሜ ማረጋገጫ ነው። ኢየሱስ በቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሰው ሁሉ በእርሱ ላይ እንደሚደርስ ይቆጥረዋል (ሐዋ 9:4-5)።

  • አብ: ወልድን ብዙ ልጆች እንዲያመጣለት፣ እነርሱም ኢየሱስን የሚመስሉ እንዲሆኑ ተልዕኮ   ሰጥቶታል (ዕብ 2:10)። አብ ሁሉን ነገር ጠቅልሎ ለልጁ ለኢየሱስ ሰጥቶታል (ዮሐ 16:15)።

  • ኢየሱስ: አባቱን ለመግለጥ (ለማስታወቅ) ወደ ምድር መጥቷል (ዮሐ17:26)።  ኢየሱስ ከአብ የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል  ስለተቀበለ መንፈስ ቅዱስን የማፍሰስ ስልጣን ተሰጥቶታል (ሐዋ 2:33፣ ዮሐ 16:7)። ኢየሱስ ተልዕኮውን ለማሳካት የሚያስፈልገውን የመስዋእትነት  ስራ ቢፈጽምም  እንኳ፣  አብ የሰጠውን ተልዕኮ ሙሉ በሙሉ ገና አልጨረሰም። የተልዕኮ ተካፋዮች አድርጎ ቤተክርስትያኑን ወደ ዓለም ምስክሮቹ አድርጎ ልኳል (ዮሐ 17:18)።

  • መንፈስ ቅዱስ: ምንም ነገር ከራሱ አይናገርም። የኢየሱስን ሀሳብ ለቤተክርስቲያን በማቀበል ኢየሱስን የሚያከብረው እርሱ ነው (ዮሐ 16:13-14)።

  • ቤተክርስቲያን: ተልዕኮዋን የምትፈጽመው ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ብቻ ነው። የቤተክርስቲያን ምስክርነት ስለ ኢየሱስ ትንሣኤና ንግስና(ጌትነት) ሊሆን ይገባል (ሐዋ 1:8)።   መንፈስ ቅዱስም ለኢየሱስ ትንሣኤና ለመንገሱ የዓይን ምስክር ሆኖ በሀይል እየተገለጠ ይሰራል።

  • ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ዘለአለማዊ ሃሳብ ማዕከላዊ ከሆነ እኛ እንዴት ልንመለከተው ይገባል?

ክፍል : ኢየሱስ ክርስቶስ ነው

  • አብ በመጀመሪያ ስለ እኛ ኢየሱስን በመስቀል ለሞት ሰጠው። በመቀጠል ኢየሱስ ከነገሠ እና ከከበረ በኋላ ለቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ ሰጠው (ኤፌ 1:22-23)።

  • ኢየሱስ በመስቀል ላይ የባሪያን መልክ ይዞ ሰዎች ማየት እስከማይፈልጉ ድረስ እጅግ ተጐሳቆለ (ኢሳ 52:14)። ከሞት ከተነሳ በኋላ  ጀምሮ እስካሁን ግን ማንም ሊደርስበት በማይችል ክብር ነግሷል።
     
  • እኛም የአይን ምስክር የሆነው መንፈስ ቅዱስ ካልመጣ በስተቀር ይህንን የከበረ ጌታ ማወቅ አንችልም (1 ቆሮ 12:3)። መንፈስ ቅዱስ በሞላን (በተቆጣጠረን) ጊዜ ግን፣ የኢየሱስ ጌትነት  ጥርት ብሎ ስለሚታየን ከአክብሮት በመነጨ መንቀጥቀጥ እንኖራለን (1 ቆሮ 2:3)።
  • ኢየሱስ ያዳነን ሊነግስብን ነው (ዘፀ 8:1)። ከአዳኝነቱ ባሻገር ኢየሱስ ጌታ ወይም ክርስቶስ (ንጉስ/ባለስልጣን/አለቃ) መሆኑን ቤተክርስቲያን እንድትቀበልና ለአለም ሁሉ እንድትመሰክር አደራን ሰጥቷታል (ሐዋ 5:42፣ ሐዋ 17:1-4፣10-11፣ ሮሜ 10:9)።
  • የኢየሱስ ጌትነት በእኛ ህይወት የሚረጋገጠው መንፈስ ቅዱስ ከእምነት የሚወለድ መታዘዝን በኛ ውስጥ  ሲያስፈጽም ነው (ሮሜ 1:1-5፣ሉቃ 6:46-48)።  ባሪያ ሳንሆን ጌትነቱን ማወቅ አንችልም።

መታዘዛችን ማቅማማት ያልተሞላና ፈጣን ሊሆን ይገባል (ዘፍ 22:3)።

  • የእምነት ማረፊያ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው የመንፈስ ቅዱስ ሃይል ነው (1 ቆሮ 2:4-5)።

  • የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከሞላብን በኋላ ሁላችንም በየሄድንበት ቦታ ክርስቶስን እንሰብካለን፤ በዚያም ታላቅ ደስታ ይሆናል (ሐዋ 8:4-8)።
  • ስለ ኢየሱስ ጌትነት ስንናገር በአእምሯችን ምንን እየሳልን ነው?

 ክፍል ፬: የጌታ ክብር ለቤተክርስቲያን ግንባታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *