ኢያሱ ጠንካራ እና መልካም መሪ ቢሆንም እንኳን እርሱን የሚተካ መሪ አላፈራም ነበር (ኢያ 13:1-2)። እርሱ ካለፈ በኋላ የተነሳዉ ትዉልድ እግዚአብሔርንም ሆነ እርሱ ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገውን ነገር የማያውቅ ስለነበረ ሁሉም በፊቱ የመሰለዉን ያደርግ ነበረ (መሳ 2:7-12)።
- በመሳፍንት መፅሀፍ በተደጋገሚ እንደምናየዉ የእግዚአብሔር ህዝብ እርሱ የሰጠዉን ቃል ኪዳን ሲተላለፍ፣እርሱን ሳይሰማ፣ ሲተዉ ቅጣት እና መርገም ይከተሉታል። ነገር ግን ህዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለዉ ግንኙነት ሲሰምር የእግዚአብሔር ጥበቃ እና ባርኮት ይበዛለታል።
- እግዚአብሔር እንደተናገረዉ ብዙ ድንቆችን አድርጎ ህዝቡን ከንዓንን አወረሳቸዉ። ህዝቡ ግን ደጋግመዉ ክፋ ስራ ሰሩ። አንዱን እግዚአብሔርን ትተዉ አምስት የአህዛብ አማልክት አመለኩ። እግዚአብሔርን ተዉ (መሳ 10:1፣ 6-9)። እንዴት እዚህ ደረጃ ደረሱ?
ሀ) ለእግዚአብሔር ታማኞች አልነበሩም።
ለ) በእግዚአብሔር አልረኩም ነበር።
ሐ) እግዚአብሔር ያደረገላቸዉን እረስተዉ ነበር።
- እግዚአብሔር ከጥፋቱ የሚመለስን ይቅር ይላል። ነገር ግን ዛሬ የዘራነዉ ዘር ነገ አድጎ ማጨዳችን የማናመልጠዉ እዉነት ነዉ።
- እኛንስ ዛሬ ምንድነዉ እግዚአብሔርን ደግመን ደጋግመን እንድንበድለዉ የሚያረገን? በመዉደቅ በመነሳት አዙሪት ዉስጥ እንድንጠመድ ያደረገን ምንድነዉ? በእጃችን ይዘነዉ ለምንዞረዉ ነገር ጊዜአችንን እንገብራለን፤ ራሳችንን አሳልፈን እንሰጣለን። ጣዖቶቻችን ፀሎት አስቁመዉናል፣ ቅዱስ ቃሉን እንዳናነብ ልባችንንና መንፈሳችንን አስረዋል፣ ከቅድስና እና ከፅድቅ አጉድለዉናል፣ ከህብረትም አስቀርተዉናል።
- በእርግጥ እግዚአብሔር ምን አጉድሎብናል? ለእርሱስ እሰከ መቼ አንታመንም?
- ምላሻችን ምን ሊሆን ይገባል? (መሳ 10:10-16)
- በእዉነተኛ ንሰሃ ለመመለስ እንወስን
- የእግዚአብሔርን ቅጣት አናቃልለዉ/አንናቀዉ
- እግዚአብሔር የሚጠላቸዉን ጣዖቶቻችንን ለማስወገድ እርምጃ እንዉሰድ