የዚህ ሳምንት መሪ ሃሳብ የሚገኘዉ በሉቃ 24:5-6 ነዉ። “ሕያው የሆነውን እርሱን ለምን ከሙታን መካከል ትፈልጋላችሁ? እርሱ ተነሥቷል! እዚህ የለም”። ሴቶቹ ለምን ሕያው የሆነውን ከሙታን መካከል ፈለጉት?
- ጌታ ኢየሱስ የተናገረዉን አለመስማታቸዉ ወይም አለማስተዋላ ቸዉ ነዉ።
- ከእዉነት ይልቅ የተመኙትን የበለጠ መፈለጋቸዉ (ማቴ 16:22)።
- እዉነትን አለመቀበላቸዉ። ሰዉ እዉነትን አለመቀበሉ ግን የእግዚአብሔርን አቋም አይለዉጥም። እግዚአብሔር ከማንም ጋር አይወግንም፤ እርሱ ብቻዉን በቃሉ ይቆማል።
- መግደላዊት ማርያም በፋሲካ በዓል፣ በማለዳ ገና ጨለማ ሳለ፣ ሽቶ ልትቀባዉ ወደ ኢየሱስ መቃብር ሄደች (ዮሐ 20:1)። ጌታ አስቀድሞ ስለ መነሳቱ የነገራትን አስተዉላ ቢሆን ኖሮ የማትጠቀምበትን ሽቶ ይዛ አትደክምም ነበረ።
- የመግደላዊት ማርያም ድካም ለጌታ ካላት ጥልቅ ፍቅር የመነጨ ነበረ። ከፍቅሯ የተነሳ የበዓሉ ፌሽታ ሳይዛት፣ የግሏ ጌታ አድርጋ ሹማዉ፣ የአይሁድን ህግ ተላልፋ አስከሬኑን ትሸከም ዘንድ ፈቀደች (ዮሐ 20:1-2፣ 11-15)።
- የማርያም ፍቅር ጌታ ኢየሱስ እራሱን እንዲገልጥ አስገደደዉ (ዮሐ 20:16)። የወደደችውን ማሪያምን የትንሳዔው የመጀመሪያዉ ምስክር አደረጋት።
- እኛስ ማልደን ተነስተን የቀናችንን በኩራት ለጌታ ሰጥተን እርሱን እንፈልጋለንን? እርሱን በእዉነት እና በፍቅር ከፈለግን፤ ብንሳሳት አንኳ አርሞ ወደ እራሱ ያቀርበናል።
- እዉነትን ልንፈልጋት የሚገባዉ በተሰጠን የእግዚአብሔር ቃል ነዉ።
- ኢየሱስ አዉነት ሆኖ ሳለ ጥቅምን፣ ምቾትን ወዘተ…አስቀድመን እዉነትን በሙታን ሰፈር ለምን እንፈልገዋለን
- ህያዉ ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት (እርዳታ) እና በቃሉ እንጠብቀዉ። እንደተናገረዉ እርሱ ተነስቷል!