እግዚአብሔር ቃል ገብቶልን በራሳችን መንገድ የገባልንን ተስፋ ያስፈፀምን ቢመስለን በረከት ሊሆንልን (ሊጠቅመን) አይችልም (ዘፍ 16:1-13) ።እግዚአብሔር የተናገረዉን በወደደዉ ሰዓት እና መንገድ እራሱ ይፈፅመዋል። “እግዚአብሔር (ያህዌ) በተናገረው መሠረት ሣራን ዐሰባት፤ የገባውንም ተስፋ ፈጸመላት። ሣራ ፀነሰች፤ ልክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ባለው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት።”-ዘፍጥረት 21:1-2
እግዚአብሔር (አገኛት)
- ሁልጊዜ ያየናል (ዘፍ 16:7፣ 16:13፣፣ ዘዳ 32:9-12፣ ”ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፣ አንተ በዚያ አለህ፤ መኝታዬንም በሲኦል ባደርግ በዚያ ትገኛለህ። በንጋት ክንፍ ተነሥቼ ብበርር፣ እስከ ባሕሩ ዳርቻ መጨረሻ ብሄድ፣ በዚያም ቢሆን እጅህ ትመራኛለች፤ ቀኝ እጅህም አጥብቃ ትይዘኛለች። እኔም፣ “ጨለማው በርግጥ ይሰውረኛል፤ በዙሪያዬ ያለውም ብርሃን ሌሊት ይሆናል” ብል፣ ጨለማ የአንተን ዐይን አይዝም፤ ሌሊቱም እንደ ቀን ያበራል፤ ጨለማም ብርሃንም ለአንተ አንድ ናቸውና።“- መዝ 139:7-12
- ዘዳ 32:9
- ለምሳሌ አጋር በፈቃድዋ ያልገባችበትን፣ አልፋ የተሰጠችበትንና የተገፋችበትን ሁኔታ እግዚአብሔር አይቷል።
- ማየት ብቻ አይደለም የፈጠረን፣ የሰራን፣ የተቤዠን እና የእራሱ ያደረገን እግዚአብሔር ፍፁም ያዉቀናል (ኢሳ 43:1-2፣ ዮሐ 10:14፣27-28)።
- አዳምና ሄዋንን ሀጢአት፣ የኤማኦስን መንገደኞችን ተስፋ መቁረጥ፣ ኤልያስን ፍርሃት፣ አጋርን ግፍ እና መገፋት አስኮብልሏቸዉ ነበር። ከስፍራችን ለቀን እንድንሄድ የሚያረገንን ነገር እግዚአብሔር ያውቀዋል እንድናዉቀዉ ም ይፈልጋል (ዘፍ 16:8፣ 3:9፣ ሉቃ 24:13-35፣ 1 ነገ 19:1-5)።
- እግዚአብሔር በእኛ ህይወት ያልጨረሰዉ ስራ ካለ ወደ ሸሸነዉ ስፍራ እንድንመለስ ሊያዘን ይችላል (ዘፍ 16:10-11፣ 1 ነገ 19:15)። ያስጨነቀንን ታግሰን በቦታችን ብንቆም ግን መዉጫን መንገድ ያዘጋጅልናል።
- እግዚአብሔርን ስናየዉ እንለወጣለን፣ እንድናለን፤ ደግሞም እናርፋለን (ዘፍ 16:13፣ ዘፍ 32:30)። እግዚአብሔር ባለበት መፍትሄአችን አለ እግዚአብሄር አይናችንን እንዲያበራና እንድናየው መጸለይ አለብን።