የፀጋ ስጦታዎች

የፀጋ ስጦታዎች

ክፍል 3

የእግዚአብሔር ጸጋ ከፍለን ልናገኘዉ የማንችለዉን ድነት እንዲሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከፈለዉ ዋጋ እንድንቀበል ያደረገን የእግዚአብሔር ጥበብ ነዉ። ከዚህም ባሻገር ጸጋን ለሰው በነፃ የተሰጠ የሚያስችል ሃይል ፣ የእግዚአብሄር ችሎታ ወይም ብቃት በማለት መተርጎም እንችላለን (ቲቶ 2:11-12)። 
ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦ ሳለ፣ ሰዉ ሁሉ ግን ይሄንን ጸጋ ተቀብሎ አይድንም። ለዚህ ጸጋ የተለያዩ ምላሾች/አመለካከቶች አሉ። እነዚህም 
ሀ) ሁለንተናዊነት (universalism): ሰዉ ሁሉ እንደገባዉ ወደ አምላኩ ጮሆ፣ በመረጠዉ መንገድ ሄዶ ይድናል። 
ለ) አካታች (inclusive): ሰዉ ለመዳን ክርስቶስ ቢያስፈልገዉም ለተገለጠለት ነገር ህሊናዉን እየታዘዘ ጥሩ ነገር ከሰራ ይድናል። 
ሐ) አንድ ብቻ መንገድ (exclusive): እንድንበት ዘንድ የተሰጠን አንድ መንገድ ጌታ ኢየሱስ ነዉ (ዮሐ 14:6፣ ሉቃ 4:12) 
የእግዚአብሔርን ጸጋ አቅለን ልናየዉ አይገባም። በአገልግሎታችን ብርቱዎች የሚያደርገን፣ ኀጢአትንና ዓለማዋዊ ምኞትን የሚያስጥለን፣ ራሳችንን እየገዛን በፅድቅ እንድንኖር የሚያስችለን የእግዚአብሔር ጸጋ ነዉ።  
ታዲያ በዚህ ጸጋ እንዴት እንኑር? 
[ነገን በተመለከተ] ይህ ጸጋ የኢየሱስን እንደገና በክብር ተመልሶ መምጣት እየጠበቅን እንድንኖር ያስተምረናል። (ቲቶ 2:12)
[ትናትናን በተመለከተ] ይህ ጸጋ ስለ ጌታ ማንነት (ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶ ከዓመፅ እንደተቤዠን) ያስተምረናል። (ቲቶ 2:14፣ ማቴ 20:8) 
[ዛሬን በተመለከተ] ይህ ጸጋ ቀን በቀን ማድረግ የሚገባንን፣ እንዲሁም በምን አይነት አመለካከት መኖር እንዳለብን ያስተምረናል። (ቲቶ 2:15) የሚሆነን ሃይል እንደውም ስለ ድነት ብቻልለ
እንደ አዳነን እየቀደሰን እና ስርአት 
[ነገን በተመለከተ] ይህ ጸጋ እንደሚያከብረን እና የኢየሱስን እንደገና በክብር ተመልሶ መምጣት እየጠበቅን እንድንኖር ያስተምረናል። (ቲቶ 2:12)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *