ሮሜ 12: 1-2
- የመጀመሪያው ለአይምሮ የሚመች አገልግሎት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት ነው ::
እግዚአብሄርን እንዴት ደስ እናሰኝዋለን 1ሳሙኤል 15:22
ስንሰማው ደስ ይሰኛል: ለጥፋትም ታልፈን አንሰጥም የሚሰማ ሰው ይታዘዛል ። እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ሆኖ በግልም በህብረትም ይናገራል ::
ድምፁን ልንራብና ልንሰማው ይገባል:: ማቴዎስ 17:5 ዮሐንስ 7:37
ህያውና ቅዱስ በሆነ መስዋአት ደስ ይሰኛል ሮሜ 6:13
እኛ ሙት ነበረን ወደ ህይወት አመጣን : በልጁ የኢየሱስ ደም ቀደሰን:: በእግዚአብሔር ፊት ህያው መሆኑን ከፈለግን ስጋችንን መግደል አለብን::
- የእግዚአብሔር አብ የእግዚአብሔር ወልድ እና የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ፈቃድ ማወቅ
2.1) የእግዚአብሔር ፈቃድ
የእግዚአብሔር ፈቃድ በጎና ደስ የሚያሰኝ ነው ገላትያ 1:4 ቆላ 2:3
እግዚአብሔር አብ ፈቃድ እኛን ከክፉ ዓለም ማዳን ነው ዮሐንስ 3:16
እግዚአብሔር ስጦታ ደስ የሚያሰኝ ነው ዕብራውያን 10:10
2.2) የወልድ ፈቃድ
ወልድ የአብን ፈቃድ ሲፈጽም መጣ ዕብራውያን 10:5-7 ሉቃስ 22 :42
2.3) የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ
የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ይመረምራል እግዚአብሔርን ይገልጣል ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔርን አውቀን ለእግዚአብሔር እንደተገባ ሆነን ለእግዚአብሔር ደስታ እንድንኖር ይረዳናል ::
ያጽናናናል ይመራናል ስለ ክርስቶስ ማድረግና ዳግም መምጣትም ያሳውቀናል::
- በልባችን መታደስ መለወጥ
የስጋን ነገር ትተን የመንፈስ ነገር ማሰብ የምንችለው በልባችን መታደስ ስንለወጥ ብቻ ነው:: ምሳሌ 22:17 ኤር 17 :19 ህዝ 26:36 ኤፌ 3:9
ይህም ለአእምሮ የሚመቸኝ አገልግሎት እንድናደርግ ይረዳናል ::