ህልዉናችን የሚረጋገጠዉ ለእግዚአብሔር ባለን ታማኝነት ነዉ by Pastor Solomon Gebre, June 16,2023

ኢያሱ ጠንካራ እና መልካም መሪ ቢሆንም እንኳን እርሱን የሚተካ መሪ አላፈራም ነበር (ኢያ 13:1-2)። እርሱ ካለፈ በኋላ የተነሳዉ ትዉልድ እግዚአብሔርንም ሆነ እርሱ ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገውን ነገር የማያውቅ ስለነበረ ሁሉም በፊቱ የመሰለዉን ያደርግ ነበረ (መሳ 2:7-12)።  ሀ) ለእግዚአብሔር ታማኞች አልነበሩም።  ለ) በእግዚአብሔር አልረኩም ነበር።  ሐ) እግዚአብሔር ያደረገላቸዉን እረስተዉ ነበር። 

ለአይምሮ የሚመች አገልግሎት                          በወንድም ፋንቱ  June 9, 2024

ሮሜ 12: 1-2  እግዚአብሄርን እንዴት ደስ እናሰኝዋለን 1ሳሙኤል 15:22 ስንሰማው ደስ ይሰኛል: ለጥፋትም ታልፈን አንሰጥም የሚሰማ ሰው ይታዘዛል ። እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ሆኖ በግልም በህብረትም ይናገራል ::  ድምፁን ልንራብና ልንሰማው ይገባል:: ማቴዎስ 17:5 ዮሐንስ 7:37  ህያውና ቅዱስ በሆነ  መስዋአት  ደስ ይሰኛል  ሮሜ 6:13  እኛ ሙት ነበረን ወደ ህይወት አመጣን : በልጁ የኢየሱስ ደም ቀደሰን:: በእግዚአብሔር […]

ሐና እና  እናትነት- By Pastor Mesfin Tilaye, May 12, 2024

ሐና እንደ ማንኛዉም ሰዉ ችግር የነበረባት ሴት ነበረች (1 ሳሙ 1:1-8)። ልጅ አልባ በመሆኗ በየዓመቱ ታዝን፣ ትጨነቅ እና ታለቅስ ነበረ።  (ሀ) ኀዘንዋን፣ ጭንቀትዋን፣ ምሬቷንና ሸክሟን በእግዚአብሔር ፊት ጣለች (1 ሳሙ 1:10)።  (ለ) እራስዋን አዋርዳ በትህትና ትፀልይ ነበረ (1 ሳሙ 1:11)።  (ሐ) እግዚአብሔር የጠየቀችዉን እስኪመልስላት ድረስ ሳታቋርጥ ትፀልይ ነበረ (1 ሳሙ 1:12)። (መ) በልቧ ትፀልይ ነበረ […]

እርሱ ተነሥቷል! – By Ameha Beyecha, May 5, 2024

የዚህ ሳምንት መሪ ሃሳብ የሚገኘዉ በሉቃ 24:5-6 ነዉ። “ሕያው የሆነውን እርሱን ለምን ከሙታን መካከል ትፈልጋላችሁ? እርሱ ተነሥቷል! እዚህ የለም”። ሴቶቹ ለምን ሕያው የሆነውን ከሙታን መካከል ፈለጉት? 

የእንደገና አምላክ – Pastor Mesfin Tilaye, April 28, 2024

አንዳንድ ጊዜ በእራሳችን ስራ ወይም አቅም ለመታመን እንፈተናለን። ጴጥሮስ ሌሎች ኢየሱስን ጥለዉ ቢሄዱ እንኳን እርሱ ከቶ እንደማይሰናከል እርግጠኛ ነበረ (ማቴ 26:33)። ደቀ መዛሙርቱም ሁሉ እንደእርሱ    እርግጠኛ ነበሩ(ማቴ 26:35)። ነገር ግን የፈተና ቀን በመጣ ጊዜ ልክ ኢየሱስ አስቀድሞ እንደተናገረዉ (ማቴ 26:31) ሁሉም ጌታን ጥለዉ ሸሹ (ማቴ 26:56)። 

እግዚአብሄር ያያል-Pastor MesfinTilaye, April 14

እግዚአብሔር ቃል ገብቶልን በራሳችን መንገድ የገባልንን ተስፋ ያስፈፀምን ቢመስለን በረከት ሊሆንልን (ሊጠቅመን) አይችልም (ዘፍ 16:1-13) ።እግዚአብሔር የተናገረዉን በወደደዉ ሰዓት  እና መንገድ እራሱ ይፈፅመዋል። “እግዚአብሔር (ያህዌ) በተናገረው መሠረት ሣራን ዐሰባት፤ የገባውንም ተስፋ ፈጸመላት። ሣራ ፀነሰች፤ ልክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ባለው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት።”-ዘፍጥረት 21:1-2 እግዚአብሔር (አገኛት)

የፀጋ ስጦታዎች

ክፍል 3 የእግዚአብሔር ጸጋ ከፍለን ልናገኘዉ የማንችለዉን ድነት እንዲሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከፈለዉ ዋጋ እንድንቀበል ያደረገን የእግዚአብሔር ጥበብ ነዉ። ከዚህም ባሻገር ጸጋን ለሰው በነፃ የተሰጠ የሚያስችል ሃይል ፣ የእግዚአብሄር ችሎታ ወይም ብቃት በማለት መተርጎም እንችላለን (ቲቶ 2:11-12)። ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦ ሳለ፣ ሰዉ ሁሉ ግን ይሄንን ጸጋ ተቀብሎ አይድንም። ለዚህ ጸጋ የተለያዩ ምላሾች/አመለካከቶች አሉ። […]