ሐና እና እናትነት- By Pastor Mesfin Tilaye, May 12, 2024
ሐና እንደ ማንኛዉም ሰዉ ችግር የነበረባት ሴት ነበረች (1 ሳሙ 1:1-8)። ልጅ አልባ በመሆኗ በየዓመቱ ታዝን፣ ትጨነቅ እና ታለቅስ ነበረ። (ሀ) ኀዘንዋን፣ ጭንቀትዋን፣ ምሬቷንና ሸክሟን በእግዚአብሔር ፊት ጣለች (1 ሳሙ 1:10)። (ለ) እራስዋን አዋርዳ በትህትና ትፀልይ ነበረ (1 ሳሙ 1:11)። (ሐ) እግዚአብሔር የጠየቀችዉን እስኪመልስላት ድረስ ሳታቋርጥ ትፀልይ ነበረ (1 ሳሙ 1:12)። (መ) በልቧ ትፀልይ ነበረ […]
እርሱ ተነሥቷል! – By Ameha Beyecha, May 5, 2024
የዚህ ሳምንት መሪ ሃሳብ የሚገኘዉ በሉቃ 24:5-6 ነዉ። “ሕያው የሆነውን እርሱን ለምን ከሙታን መካከል ትፈልጋላችሁ? እርሱ ተነሥቷል! እዚህ የለም”። ሴቶቹ ለምን ሕያው የሆነውን ከሙታን መካከል ፈለጉት?
የእንደገና አምላክ – Pastor Mesfin Tilaye, April 28, 2024
አንዳንድ ጊዜ በእራሳችን ስራ ወይም አቅም ለመታመን እንፈተናለን። ጴጥሮስ ሌሎች ኢየሱስን ጥለዉ ቢሄዱ እንኳን እርሱ ከቶ እንደማይሰናከል እርግጠኛ ነበረ (ማቴ 26:33)። ደቀ መዛሙርቱም ሁሉ እንደእርሱ እርግጠኛ ነበሩ(ማቴ 26:35)። ነገር ግን የፈተና ቀን በመጣ ጊዜ ልክ ኢየሱስ አስቀድሞ እንደተናገረዉ (ማቴ 26:31) ሁሉም ጌታን ጥለዉ ሸሹ (ማቴ 26:56)።
እግዚአብሄር ያያል-Pastor MesfinTilaye, April 14
እግዚአብሔር ቃል ገብቶልን በራሳችን መንገድ የገባልንን ተስፋ ያስፈፀምን ቢመስለን በረከት ሊሆንልን (ሊጠቅመን) አይችልም (ዘፍ 16:1-13) ።እግዚአብሔር የተናገረዉን በወደደዉ ሰዓት እና መንገድ እራሱ ይፈፅመዋል። “እግዚአብሔር (ያህዌ) በተናገረው መሠረት ሣራን ዐሰባት፤ የገባውንም ተስፋ ፈጸመላት። ሣራ ፀነሰች፤ ልክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ባለው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት።”-ዘፍጥረት 21:1-2 እግዚአብሔር (አገኛት)
የፀጋ ስጦታዎች
ክፍል 3 የእግዚአብሔር ጸጋ ከፍለን ልናገኘዉ የማንችለዉን ድነት እንዲሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከፈለዉ ዋጋ እንድንቀበል ያደረገን የእግዚአብሔር ጥበብ ነዉ። ከዚህም ባሻገር ጸጋን ለሰው በነፃ የተሰጠ የሚያስችል ሃይል ፣ የእግዚአብሄር ችሎታ ወይም ብቃት በማለት መተርጎም እንችላለን (ቲቶ 2:11-12)። ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦ ሳለ፣ ሰዉ ሁሉ ግን ይሄንን ጸጋ ተቀብሎ አይድንም። ለዚህ ጸጋ የተለያዩ ምላሾች/አመለካከቶች አሉ። […]