ክፍል አንድ
የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታዎች በክርስቶስ ኢየሱስ ለምናምን ሁሉ የተሰጡ ናቸዉ (1 ጴጥ 4:10)።
የፀጋ ስጦታዎችን ለምን ተቀበልን?
-
እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲከብር ነዉ (1 ጴጥ 4:11)
-
ቤተክርስትያን እንድትታነፅ (ቅዱሳን ወደ ክርስቶስ ሙላት እንዲደርሱበት) ነዉ (1 ቆሮ 12:7፣ 1 ቆሮ 14:2፣ 1 ጴጥ 4:10)
-
እንደ አንድ አካል ያለ መበላለጥ በአንድነት እንድንኖር ነዉ (1 ቆሮ 12:14-30)
-
የእግዚአብሔርን ትልቅነት በመግለጥ የሰዉን ልብ ለወንጌል ለመክፈት ነዉ (ማር 16:20)
1 ቆሮንቶስ 12:8-10
-
ሶስት የመገለጥ ስጦታዎች (የጥበብን ቃል መናገር፣ የዕውቀትን ቃል መናገር እና መናፍስትን መለየት)፣
-
ሶስት የሀይል ስጦታዎችን (እምነት፣ ፈዉስ እና ታምራትን የማድረግ)፣
-
ሶስት የንግግር ስጦታዎች (ትንቢትን የመናገር፣ በልዩ ልዩ ልሳን የመናገር እና በልዩ ልዩ ልሳን የተነገረውን የመተርጐም)