Logo2

የፀጋ ስጦታዎች

የፀጋ ስጦታዎች

ክፍል አንድ

የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታዎች በክርስቶስ ኢየሱስ ለምናምን ሁሉ የተሰጡ ናቸዉ (1 ጴጥ 4:10)።

የፀጋ ስጦታዎችን ለምን ተቀበልን?

  1. እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲከብር ነዉ (1 ጴጥ 4:11)

  2. ቤተክርስትያን እንድትታነፅ (ቅዱሳን ወደ ክርስቶስ ሙላት እንዲደርሱበት) ነዉ (1 ቆሮ 12:7፣ 1 ቆሮ 14:2፣ 1 ጴጥ 4:10)

  3. እንደ አንድ አካል ያለ መበላለጥ በአንድነት እንድንኖር ነዉ (1 ቆሮ 12:14-30)

  4. የእግዚአብሔርን ትልቅነት በመግለጥ የሰዉን ልብ ለወንጌል ለመክፈት ነዉ (ማር 16:20)

1 ቆሮንቶስ 12:8-10

  • ሶስት የመገለጥ ስጦታዎች (የጥበብን ቃል መናገር፣ የዕውቀትን ቃል መናገር እና መናፍስትን መለየት)፣

  • ሶስት የሀይል ስጦታዎችን (እምነት፣ ፈዉስ እና ታምራትን የማድረግ)፣

  • ሶስት የንግግር ስጦታዎች (ትንቢትን የመናገር፣ በልዩ ልዩ ልሳን የመናገር እና በልዩ ልዩ ልሳን የተነገረውን የመተርጐም)

ሀ) የዕውቀትን ቃል መናገር:-  ከሰዉ ነባር ዕዉቀት፣ የተፈጥሮ ችሎታ፣ ትምህርት ያልመነጨ መንፈስ ቅዱስ የሚያቀብለን መገለጥ ነዉ። ዓላማዉም ሰዎችን ማገልገል፣ መርዳት ብሎም ወደ ኢየሱስ ማድረስ ነዉ (ዮሐ 4:7-29)

ለ) የጥበብን ቃል መናገር:- የተገለጠ ዕዉቀትን እንዴት እንደምንናገር የምናዉቅበት፣ ሰዎችን ሳንሰብር አቃንተን ለእግዚአብሔር ገንዘብ የምናደርግበት፣ መፍትሄ ለጠፋባቸዉ የህይወት ጉዳዮች ሰዎች እንዴት ማለፍ እንደሚችሉ መፍትሔ የምናሳይበት ፀጋ ነዉ

(2 ሳሙኤል 12 ፣ ዮሐ 8:3-11)

ሐ) መናፍስትን የመለየት: ከክንዉኖች ጀርባ ያሉትን መናፍስት ከሰዉከአጋንንት ወይም ከእግዚአብሔር መሆናቸዉን (ምንጫቸዉን) ለይተን የምናውቅበት ፀጋ ነዉ (1 ዮሐ 4:1፣ ማቴ 16:15-23፣ ሐዋ 5:1-4)።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Subscribe for News