Logo2

የፀጋ ስጦታዎች

የፀጋ ስጦታዎች

ክፍል ሁለት

የጸጋ ስጦታዎችን እንዴት እንለይ?

  1. አጥብቀን በመፀለይ

  2. በተደጋጋሚ ወደ ውስጣችን የሚመጡ ነገሮችን ማስተዋል

  3. በትንሽ ህብረቶች ውስጥ ፀጋን በመግለጽ መለማመድ

  4. የተገለጠ ፍሬን ማየት

  5. የቅዱሳንን ምስክርነት መስማት በተለይ ከመሪዎች

የጸጋ ስጦታ አይነቶች

  1. የሃይል ስጦታዎች እግዚአብሔር ሃይሉን የሚገልጥባቸው የፀጋ ስጦታዎች ናቸው እነርሱም እምነት: ተአምራትን ማድረግና ፈውስ ናቸው ። 

1.1) የእምነት ስጦታ

ሀ. የመዳን እምነት:- ያለ እምነት መዳንም እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘትም አይቻልም።

በስራ ሳይሆን በእምነት ድናችኋል ኤፌ 2:8

ለ. የእምነት ስጦታ

የእምነት ስጦታ ያለው ሰው ሁኔታውን ሳይሆን በእግዚአብሔር ሃሳብ ውስጥ ያለውን ነገር ፣  ማየት ይችላል::

2 ነገ3:9-18

1.2) የፈዉስ ስጦታ:

 አዳም አስቀድሞ ሲፈጠር በስጋም በነፍስም በመንፈስም በሙሉ ጤንነት ውስጥ ነበረ::  በሀጥያት ምክንያት ግን በሽታ ወደ ዓለም ገባ: በሽታ አካላዊ ብቻ አይደለም ስነልቡናዊም እንዲሁም መንፈሳዊም ነው:: በመፀሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሀዋሪያቱን እየሱስም  ህመምተኞችን ይፈውሱ ነበር:: ሐዋ 5:12-16 ያቆ 4:5-16 ሐዋ 9:32-35 

ስጦታው የተሰጠ ቢሆንም በእግዚአብሔር ሀሳብና ጊዜ የሚገለጥ ነው::

1.3) የታምራት ስጦታ :- የተፈጥሮ ህግ ሽሮ ወይም አልፎ ህዝቡን ለመርዳት እግዚአብሔር የሚያደርገው ድንቅ  ነገርነው:: ዘዳ 8:4 ሐዋ 9:42

  1. የንግግር ስጦታዎች : እግዚአብሔር ለህዝቡ የሚናገርባቸው መንገዶች ናቸው እነርሱም በልሳን መናገር: በልሳን የተነገረን መተርጎምና: ትንቢት ናቸው

2.1) ልሳን የመናገርና የመተርጎም :- ልሳንን የሚናገር እራሱን ያነፃል ::

ልሳን:- እግዚአብሔር ባልተማርነው በማናቀው ቋንቋ መንፈስን ሞልቶ ሲያናገረን ነው:: የሚተረጎም ከሆነ ግን ጉባኤን ያንጻል::

2.2) ትንቢትን መናገር :- ትንቢት እግዚአብሔር ሰውንለማነጽ ለመምከር ለማጽናናት የሚናገረው ነው :: የትንቢት ውጤት ከነዚህ ውጪ ከሆነ ከእግዚአብሔር ያልሆነ ስለሆነ ሊመረመር ይገባል:: ትንቢትን ልንንቅ ሳይሆን ልንመረምር ይገባናል :: ቆሮንቶስ 14:1 ቆሮንቶስ 14:26

እነዚህ ሁሉ የተሰጡን የፀጋ ስጦታዎች ዓላማቸው ለቤተ ክርስቲያን ብልቶች ጥቅምና ሰዎች ወደ ጌታ እርሱን እንዲመለከቱ ነው::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Subscribe for News