ክፍል ሁለት
የጸጋ ስጦታዎችን እንዴት እንለይ?
-
አጥብቀን በመፀለይ
-
በተደጋጋሚ ወደ ውስጣችን የሚመጡ ነገሮችን ማስተዋል
-
በትንሽ ህብረቶች ውስጥ ፀጋን በመግለጽ መለማመድ
-
የተገለጠ ፍሬን ማየት
-
የቅዱሳንን ምስክርነት መስማት በተለይ ከመሪዎች
የጸጋ ስጦታ አይነቶች
-
የሃይል ስጦታዎች እግዚአብሔር ሃይሉን የሚገልጥባቸው የፀጋ ስጦታዎች ናቸው እነርሱም እምነት: ተአምራትን ማድረግና ፈውስ ናቸው ።
1.1) የእምነት ስጦታ
ሀ. የመዳን እምነት:- ያለ እምነት መዳንም እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘትም አይቻልም።
በስራ ሳይሆን በእምነት ድናችኋል ኤፌ 2:8
ለ. የእምነት ስጦታ
የእምነት ስጦታ ያለው ሰው ሁኔታውን ሳይሆን በእግዚአብሔር ሃሳብ ውስጥ ያለውን ነገር ፣ ማየት ይችላል::
2 ነገ3:9-18
1.2) የፈዉስ ስጦታ:
አዳም አስቀድሞ ሲፈጠር በስጋም በነፍስም በመንፈስም በሙሉ ጤንነት ውስጥ ነበረ:: በሀጥያት ምክንያት ግን በሽታ ወደ ዓለም ገባ: በሽታ አካላዊ ብቻ አይደለም ስነልቡናዊም እንዲሁም መንፈሳዊም ነው:: በመፀሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሀዋሪያቱን እየሱስም ህመምተኞችን ይፈውሱ ነበር:: ሐዋ 5:12-16 ያቆ 4:5-16 ሐዋ 9:32-35
ስጦታው የተሰጠ ቢሆንም በእግዚአብሔር ሀሳብና ጊዜ የሚገለጥ ነው::
1.3) የታምራት ስጦታ :- የተፈጥሮ ህግ ሽሮ ወይም አልፎ ህዝቡን ለመርዳት እግዚአብሔር የሚያደርገው ድንቅ ነገርነው:: ዘዳ 8:4 ሐዋ 9:42
-
የንግግር ስጦታዎች : እግዚአብሔር ለህዝቡ የሚናገርባቸው መንገዶች ናቸው እነርሱም በልሳን መናገር: በልሳን የተነገረን መተርጎምና: ትንቢት ናቸው