Logo2

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ በሁለት አበይት ነገሮች ዙሪያ ተምረናል

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ በሁለት አበይት ነገሮች ዙሪያ ተምረናል

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ በሁለት አበይት ነገሮች ዙሪያ ተምረናል 

1. መንፈስ ቅዱስ ከሰዎች ጋር ሶስት መሰረታዊ  ግንኙነቶች አሉት

 

 (ሀ) ዮሐ 3:3-6- ዳግም ልደት የሚገኘዉ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነዉ። 
 (ለ) ሮሜ 8:9፣ 1 ቆሮ 6:19፣ ገላ 4:6- ክርስቶስ እየሱስን አምነዉ ዳግም በተወለዱት ሁሉ ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ይኖራል። 
(ሐ) 1 ቆሮ 12:7-11፣ ሮሜ 12:6-8-  ቤተክርስትያን በፀጋ ስጦታዎች የሚሞላዉ መንፈስ ቅዱስ ነዉ። መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን የሚያድለዉ ለየግል ጥቅማችን ሳይሆን ቤተክርስትያን እንድትታነፅ (ሌሎች እንዲያድጉ፣ እንዲታረሙ፣ እንዲፅናኑበት እና ወደ ክርስቶስ ሙላት እንዲደርሱበት) ነዉ። 

 

 

 

 

2. [የስጦታዎች ባለቤት] መንፈስ ቅዱስ ማነዉ?

 

 

 

 

መንፈስ ቅዱስ እንደ አብ እና ወልድ ከስላሴ አካላት አንዱ የሆነ እግዚአብሔር ነዉ።  መንፈስ ቅዱስ ሀይል አይደለም። ነገር ግን የእራሱ የሆነ ማንነት እና ዘለዓለማዊ አካላዊ ህልዉና ያለዉ አምላክ ነዉ። ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ የእራሱ የሆነ ዕዉቀት (1 ቆሮ 2:10-12፣ ሮሜ 8:27፣ ዮሐ 14:26፣ ነህ 9:20)፣ ስሜት (ኤፌ 4:30፣ ኢሳ 63:10፣ መዝ 106:32-33)፣ እና ፈቃድ (ሐዋ 16:6-7፣ 1ቆሮ 12:11፣ 2ጴጥ 1:20-21) አለዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Subscribe for News